bih.button.backtotop.text

አንድ ዶክተር የጡት ካንሰርን እንዴት እንደሚመረምር

የጡት ካንሰርን አስቀድሞ መመርመሩ አስፈላጊ ነው ፣ ይህም በመደበኛነት የማሞግራም ምርመራ በማድረግ ሊከናወን ይችላል ፡፡ ምርመራውን ከዚህ ቀድም አድርገውት የማያውቁ ከሆነ ፣ በጡት ካንሰር ምርመራ ወቅት ሊጠብቁት የሚችሉት ነገር የሚከተለውን ይሆናል፦

በሴቶች ላይ በምርመራ ከሚገኙ የካንሰር ዓይነቶች መካከል የጡት ካንሰር በጣም የተለመደው ነው ፡፡  ሆኖም የጡት ካንሰርን አስቀድሞ በመመርመር እና ትክክለኛውን የክትትል ሕክምና በማግኘት ህይወትዎን የማትረፍ እድልዎን በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምሩት ይችላሉ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የጡት ካንሰር፣ ልክ እንደ ማንኛውም በሽታ ለማከም ቀላል እንዲሁም የህክምናው ስኬት ደረጃ  ዘግይቶ ከመገኘቱ ይልቅ በቅድሚያ ሲታውቅ ከፍተኛ ስለሆነ ነው።.

ማሞግራም የጡት ካንሰርን ለመጠቆም ይጠቅማል፡፡ ማሞግራም የኤክስ-ሬይ(x-ray) ምስልን በመጠቀም የሁለቱም ጡቶች ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ ጤናማ ያልሆኑ እብጠቶችን/ነገሮችን የሚጠቁም የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ነው ፡፡ ሊገኙ የሚችሉት ጤናማ ያልሆኑ ነገሮች የሚያጠቃልሉት ፦ ጥቃቅን የካልሲየም ቅንጣቶች፤ ውሀ የቋጠሩ እባጮች እና እጢዎች ሲሆኑ የራስን ጡት በራስ በሚመረምሩ ወቅት ምናልባትም ሳይስተዋሉ ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ የጡት ካንሰር ካለብዎ ለማወቅ ማሞግራም የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡

ሁለት አይነት ማሞግራምዎች አሉ ፡፡ እነሱም፦  የማጣሪያ እና የምርመራ ማሞግራም ናቸው፡፡ መደበኛው የማጣሪያ ማሞግራም የሚደረገው ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት ላልታየባቸው ሴቶች ሲሆን የሚያስፈልጉት ጥቂት ምስሎች ስልሆኑ የሚወስደው ጊዜ አጭር ፡፡ በሌላ በኩል ፣ የምርመራው ማሞግራም ዶክተሩ/ ሯ ትክክለኛውን ምርመራ እንዲያደርግ/ እንድታደርግ  በተለያዩ ማዕዘኖች እና የማጉያ መጠኖች ብዙ ምስሎች ያስፈልጉታል ፡፡ ይህ የሚሆነው ሴቶች ጡታቸው ላይ ህመም ሲሰማቸው ፣ ጠጣር እብጠት ሲያስተውሉ  ወይም በማጣሪያው ማሞግራም ላይ የእብጠት ምልክት ሲገኝ ነው ፡፡

ምርመራ በሚካሄድበት ቀን የሕክምና ታሪክዎን የሚዘረዝር ቅጽ እንዲሞሉ እና ያልተለመዱ ምልክቶች ከአለዎት እንዲገልፁ ይጠየቃሉ ፡፡.

ከዚያ ወደ የግል ታካሚ ክፍል ይወሰዱ እና ከወገብ በላይ ያሉትን ጌጣጌጥ እና አልባሳት ሁሉ እንዲያወልቁ ይነገሮታል ፡፡ ሰውነትዎንም የሚሸፍኑበት ሽርጥ ይስጦታል ፡፡  በነርስ እርዳታ በልዩ የማሞግራም ማሽን ፊት በቁመትዎት ልክ መስታካከል በሚችል የማሽኑ ጠፍጣፋ የጡት ማሳረፊያ ቦታ ላይ ጡትዎን በአግድም ያስተኙታል፡፡ ሁለተኛ የማሽኑ ጠፍጣፋ አካል ጡትዎትን ከላይ ውደታች ተጭኖ ይቀመጣል ፣ ይህም የኤክስ-ሬይ ምስሉ ከመነሳቱ በፊት ጡትዎን ለመዘርጋት እንዲሁም ውፍረቱ ከአንድ ጎን ወደ ሌላው እንዳይዛባ እና እይታው እንዳይንጋደድ ያደርገዋል።.

በሂደቱ ወቅት (ለጥቂት ሰከንዶች ብቻ) ፣ ፍፁም ሳይንቀሳቀሱ ቆመው እስትንፋስዎን እንዲይዙ ይጠየቃሉ። ማሽኑ ጡቶት ላይ የሚፈጥረው ጫና ምቾት ሊነሳ ይችላል። ህመም ከተሰማዎት ግን ማስተካከያዎች እንዲደረጉሎት ነርሷን ያሳውቁ፡፡
ከማሞግራምዎ በኋላ ማንኛውም ያልተለመዱ ምልክቶች ካሉ በሐኪምዎ ብዙም ሳይቆይ ሊነግርዎት ይችላል ፡፡ እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ እንደ ተጨማሪ ምርመራዎች ፣ ክትትል ወይም ህክምናዎች ያሉ መውሰድ ያለባቸውን ቀጣይ እርምጃዎች ይነገርዎታል።
 ከሐኪምዎ ጋር ለመወያየት እና ስለ ሰውነትዎ የበለጠ ለመማር - ይህም ጤናማ የሆነውን ለማወቅ እና ጡቶችዎን በተመለከተ ማናቸውንም ከጤናማው የተዛቡ ምልክቶችን ለመረዳት ጊዜውን መጠቀም ይችላሉ ። ከሐኪማቸው ጋር ለመነጋገር ምቾት የሚሰማቸው ሴቶች አስጊ ምልክቶችን ችላ የማለት እድላቸው አነስተኛ ሲሆን ማንኛውንም ችግር ከተጠራጠሩ ከሐኪማቸው ጋር የመገናኘት እድላቸውም ከፍተኛ ነው ፡፡

ዕድሜያቸው በ40 ዓመት አካባቢ የሆኑ ሴቶች በቀጠሮ የመጀመሪያውን የመነሻ ማሞግራም እንዲያድርጉ ከዛም በዓመት ወይንም በየሁለት ዓመቱ እንዲመረመሩ ይበረታታሉ ፡፡ ሆኖም በጡት ካንሰር የመያዝ ከፍተኛ አጋጣሚ ያላቸው  ሴቶች፣ ለምሳሌ የጡት ካንሰር የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው ሴቶች ወይም በአንዱ ወይም በሁለቱም ጡቶች ላይ ያልተለመደ እብጠት ያስተዋሉ ሴቶች በፍጥነት ማሞግራም ማድረግ ይኖርባቸዋል ። ማሞግራም በየስንት ጊዜው ለማድረግ  እንደሚመከር ከሐኪምዎ ጋር ይወያዩ፡፡

በዶክተር ዋንቻለም ኑንቪቲፖንግ ፣ ልዩ የጡት ቀዶ ጥገና ሀኪም ፣ ከቀዶ ጥገና ክሊኒክ ፣ በምሩንግራድ ሆስፒታል የተዘጋጀ

ስለ ጡት ካንሰር ምርመራ የበለጠ ማወቅ እፈልጋለሉ? - ጥያቄ ጠይቁን
በጡት እንክብካቤ ክሊኒክ ውስጥ ከጡት ካንሰር ስፔሻሊስት ጋር ቀጠሮ መያዝ እፈልጋሉ? ቀጠሮ ይያዙ
For more information please contact:

Related Health Blogs