bih.button.backtotop.text

ልብ ከፍቅርም የላቀ ነገር አለው

 “የፍቅር የፈውስ ኃይል" የሚለው ሐረግ ከፍቅር ልብ ወለድ ላይ የተወሰደ የተለመደ አባባል ሊመስል ይችላል ፣ ግን ይህንን በግልጽ የሚደግፉ ብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንዳሉ ያውቃሉ? የፍቅር ፣ የጓደኝነት ወይም ከቤት እንስሳ ጋር ያሉ መልካም ግንኙነቶች መልካም ጤናን፣ በተለይም ከልብ ጤና ጋር በተያያዘ ፤ የልብ የደም ስር (cardiovascular) በሽታዎችን እና በልብ ምክንያት የሚከሰት ሞትን በመቀነስ ረገድ  ጤናን በመደገፍ ሚና ይጫወታሉ ።

እንደ አድናቆት ፣ በፍቅር መውደቅ  ወይም የመጀመሪያ አዎንታዊ እይታን ለመሳሰሉ ስሜቶች ብዙውን ጊዜ እውቅናው ለልብ ቢሰጥም እውነቱ ግን እነዚህ ስሜቶች የሚጀምሩት በአንጎል ውስጥ መሆኑ ነው ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ አንጎል እንደ አድረናልን እና ኖረፕነፍርን የሚባሉ ሆርሞኖችን ያመነጫል ፡፡ ፍቅር ሲይዘን አክሲቶስን የተባለው አጣማሪ ሆርሞን መመንጨት ይጀምራል ፡፡ እነዚህ ሁሉ ሆርሞኖች በቀሪው የሰውነት ክፍል ላይ የፊዚዮሎጂያዊ ተፅዕኖ አላቸው ፣ ይህም ልብ በፍጥነት እንዲመታ እና የደም ሥሮች እንዲሰፉ ፣ የደም ዝውውርን እና አጠቃላይ የልብ አሰራር እንዲሻሻል ያደርጋሉ ፡፡

ረጋ ያለ የአካል ንክኪ ፣ ዓይን ለዓይን መተያየት ፣ በስምምነት የሚደረጉ ውይይቶች ወይም ሌላው ቀርቶ ስለ የሚወዷቸው ሰዎች ማሰብ ብቻ በአካልዎ ሁኔታ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖን ያሳድራሉ ፡፡ የተሻሻለ የልብ አሰራር እና ከዚህያ ጋር ተያይዞ ያለው የደም ሥሮች መለጠጥ የደም ግፊት ላለባቸው ሰዎች ወይም በደም ሥሮች መጥበብ  ለሚጠቁ ሰዎች በጣም ጠቃሚ ናቸው ፡፡

ከፊዚዮሎጂያዊ ጥቅሞች በተጨማሪ ፍቅር የባህሪ ጥቅሞችም አሉት ፡፡ በብርግም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የኒውሮሳይንስ እና የስነ-ልቦና ባለሙያ እና ተመራማሪ ዶክተር ጁሊያን ሆልት-ላንስታድ ከ300,000 በላይ ሰዎችን እንደ ናሙና በመውሰድ ጥናት አድርገዋል  ፡፡ በ ‹PLOS› ሜዲካል መጽሔት የታተመው የተመራማሪዋ ግኝቶች እንደሚጠቁሙት ከእኛ ጋር የቅረብ ግንኙነተት ያላቸው ሰዎች ቀና ባህሪ እንዲኖረን የሚያደርግ ከፍተኛ ተፅዕኖ አላቸው፡፡ ይህ ጤናማነት በማይሰማን ጊዜ የሞራል ድጋፍ በመስጠት ሊገለጥ ይችላል ፣ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንድናደርግ እና ጤናማ ምግብ እንድንመገብ ያበረታታናል ፡፡ በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ ያሉ አዎንታዊ ግንኙነቶች ልክ ሲጋራ ማጨስን እንደማቆም ያህል ለጤንነታችን ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ ማለትም ይቻላል ።
 
ከአሜሪካ ብሔራዊ የጤና መረጃ ማዕከል የተገኘው አኃዛዊ መረጃ እንደሚያሳየው ያገቡ ሰዎች ካላገቡ ፣ ከተፋቱ ወይም የትዳር አጋራቸውን በሞት ካጡ ሰዎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ፡፡ ነገር ግን ወደ ልብ ጉዳዮች በሚመጣበት ጊዜ ጥራት በማንኛውም ጊዜ ከብዛት ወይም የግንኙነት ድረጃ/ሁኔታ ይበልጣል፡፡ ጤናማ እና እርካታ ያለው ግንኙነት ያላቸው ያልተጋቡ ፍቅረኛሞች ከፍቅር አልባ እና ፍላጎትን ባላሟሉ ትዳር ውስጥ ካሉ ሰዎች በተሻለ የጤና ደረጃ አላቸው ፡፡ ነገር ግን ገና በፆታዊ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ካልሆኑ አይጨነቁ ፡፡ ከቅርብዎ ካሉ ስዎች ጋር ፣ ከቤተሰብዎ ፣ ከጓደኞችዎ  ከቤት እንስሳትዎ ጋር  ያለ መልካም ግንኙነቶች ሳይቅር እንኳ የልባችንን ጤና ያሻሽላሉ ። በሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው በነበሩ የደም ሥር የልብ ህመም ታካሚዎች ላይ የተደረገ አንድ የስዊድን ሀገር ጥናት ፤ አንዳንድ ልብን የሚነኩ ግኝቶችን አሳይቷል ፡፡ ውሾች ያሏቸው ታካሚዎች ብቻቸውን ከሚኖሩ ታካሚዎች ይልቅ ከሆስፒታል ከወጡ በኋላ የመሞት አጋጣሚያቸው  67%  ዝቅ ያለ ነው ፡፡ ወደ ሆስፒታሉ በተዳጋጋሚ የመሄድ አጋጣሚያቸውም  እንዲሁ ብቻቸውን ከሚኖሩት ይልቅ ያነሰ ነበር ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ባለ አራት እግር ጓደኞቻቸው እነዚህን ታካሚዎች ለተወሰነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲወጡ እንዲሁም ከቤት ሲወጡ ከተዋወቋቸው ሰዎች ጋር መስተጋብር እንዲፈጥሩ እና ግንኙነቶች እንዲገነቡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላደረጉ ነው ፡፡ ይህን ስንል ማንኛውም የቤት እንስሳት ዝርያ በባለቤቶቻቸው ልብ ላይ አዎንታዊ እና የሚያረጋጋ ውጤት አላቸው ማለት ነው ፡፡

መልካም ግንኙነቶችን አስቅድሞ መገንባት ጥሩ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንትም ሊሆን ይችላል ፡፡ በዓለም ላይ ረዥሙ ሳይንሳዊ ጥናት የሃርቫርድ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሮበርት ዋልዲንገር በወጣቶች እድገት ላይ ያደረጉት ጥናት ነው ። ጥናቱ እ.ኤ.አ. ከ 1938 ጀምሮ ለ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል በሁለት የናሙና ቡድን ተከፍሎ የሰዎችን ሕይወት ተከታትሏል ። ከዋና ዋና የጥናቱ ግኝቶች መካከል አንዱ ከሌሎች ከሚታወቁት ውሳኝ ነገሮች መካከል ፤ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ እያሉ መልካም ግንኙነቶችን መመስረት በእርጅና ዘመን የመልካም የጤና ሁኔታ ጠቋሚ እንደሆነ ነው ፡፡  ይህም ከኮሌስትሮል መጠን እንኳን በተሻለ ሁኔታ  የመልካም ጤና ጠቋሚ ነው ።

በፍቅር ወር በበምሩንግራድ ሆስፒታል የሚገኘው የልብ ማዕከል ሁሉም ሰው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከማድረግ ጥሩ ምግብን ከመመገብ እና መደበኛ የጤና ምርመራ ከማድረግ ባለፈ ልቡን እንዲንከባከብ በጣም ይፈልጋል ፡፡ እንደ የግል እንክብካቤዎ አንድ አካል ሆኖ የሚካተት ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ጋር  መልካም ግንኙነት የመመስረት እና የመደሰቻ ጊዜው አሁን ነው ። እኛም በሙሉ ልባችን ልብዎን ለመንከባከብ ዝግጁ መሆናችን እንዲውቁልን እንፈልጋለን ፡፡
For more information please contact: