bih.button.backtotop.text

ፅናት ካለ፣ መንገድ አለ ፡ በፅናት ካንሰርን መታገል

በመልካም ሐኪም እጅ ውስጥ  ከመሆን በተጨማሪ የአምሮ ሀይል / የአስታሰብ ጠንካራነት  ካንሰርን ለመጋፈጥ ወሳኝ ነገር ሊሆን ይችላል ፡፡ ተስፋ ማድረግ ፅናት እና ከመቋቋም አቅም ጋር ሲሆን መልሶ የማገገሚያ ጎዳና ላይ ስኬታማ ለመሆን አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይችላል። በዚህ ዓመት የዓለም የካንሰር ቀን ፣ በምሩንግራድ ሆስፒታል የሆራይዘን ክልላዊ የካንሰር ማዕከል የካንሰር ህሙማንን የመንከባከብ ፍቃደኝነታቸንን በማወጅ  “ ነኝ ፤ እናም እሆናለሁ” ከሚለው መሪ ቃል ጋር ተያይዞ ፅናትን በማጠናከር ላይ ይሳተፋል  ፡፡ ተስፋ ከፅናት ጋር ተደምሮ ፤ ከሌሎች ጋር የማይመሳሰል/ ከሌላ ነገር የተሻለ ሀይል አለው ፡፡


ከተራቀቀ የህክምና ቴክኖሎጂ ባሻገር የካንሰር በሽታን ለመጋፈጥ በሚደረገው ትግል ውጤታማ ከሆኑ መሳሪያዎች መካከል አንዱ ፅናት ነው ። በሕክምናው ወቅት መሰናክሎችን ማለፍ ይቅርና ደፍሮ የአካል እንዲሁም ሌሎች ምርመራዎችን ለማደረግ ትልቅ ፅናት ይጠይቃል ፡፡ የቤተሰብ እንዲሁም የወዳጅ ፍቅርን  ከግምት ውስጥ አስገብቶ ወደ ጥንካራ ለመሆን ፅናትን ይጠይቃል ። ከ 2000 ዓመታት በፊት ፕሌቶ በሰውነት እና በአዕምሮ መካከል ያለውን ጥልቅ ትስስር በመጥቀስ ፣  “ አጠቃላዩን ባለማወቃቸው ምክንያት ነው ። አጠቃላዩ ደህና ካልሆነ በስተቀር ከፊሉ በጭራሽ ደህና ሊሆን አይችልም" ሲል እንደተናገረው ማለት ነው ። የአንድ ሰው መልካም ጤንነት የጤናማ አዕምሮ እና የጤናማ አካል የተጠላለፈ ጥምረት ውጤት ነው ሊባል ይችላል።

 
ለመመርመር የመድፈር  ‘ቆራጥነት’
አሃዛዊ ጥናት እንደሚያሳየው በአንድ ዓመት ውስጥ በዓለም ዙሪያ ወደ 18 ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ የካንሰር ኬዞች ይገኛሉ ፡፡ ቁጥሩ አስደንጋጭ ቢሆንም ከ 40% በላይ የሚሆነውን ካንሰር መከላከል የሚቻል ሲሆን በህይወት የመትረፍ ቁጥሩም ከፍተኛ ነው ፡፡ የራስ ጤንነት መንከባከብ እና መደበኛ ምርመራ ማድረግ ቀደሞ በሽታውን ለማግኘት እና  ካንሰሩን ከምንጩ ለማድረቅ ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡ ለምሳሌ ፣ የጡት ካንሰር በማሞግራም ምርመራ በቀላሉ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያ ደረጃ  እያለ  ከተደረሰበት  በ 5 ዓመት ውስጥ የህይወት የማትረፍ አጋጣሚው ከ 99-100% ነው ፡፡


ጽኑ የመሆን “ቆራጥነት”
 
Tin-May-Lwin_Paint.jpg
 
በዘመናዊ ህክምና በመታገዝ አዕምሮም በከፍተኛ ውጤት ካንሰርን ለመዋጋት ድንቅ አገልግሎት ሊኖረው ይችላል ። ለማገገም የመጀመሪያው እርምጃ የታካሚው በተስፋ ለመኖር የምርጫ ጽናት ነው ። ከ 20 ዓመታት በላይ ሲታገሉ የቆዩት ከያንጎን የመጡት የኮምፒዩተር ጥናት የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ቲን ሜይ ሊዊን እንደተናገሩት “የአዕምሯችን ሁኔታ ለሕክምናው ሂደት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡ እንድናለን ብለን ካመንን እንድናለን፡፡ እመነኝ, እንደማትድን ካሰብክ, አትድንም.  ፡፡ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር መርጫለሁ ፡፡ ምንም እንኳን በወቅቱ በልብ ህመም እንዲሁም በስኳር ህመም በተጨማሪ ታምሜ የተሰቃየሁ ቢሆንም ደስታዬን እንዲነጠቁኝ አልፈቀድኩም.

ይህ ፅናት ካንሰሩ ወደሚወዷቸው በቤተሰብ አባል ላይ ተመልሶ ቢመጣም እንኳን ጠንክሮ ወደፊት የመገስገስ  ፍላጎትን ይጨምራል ። ይህ ነበር የተከሰተው በካምቦዲያዊትዋ  ነጋዴ  ስሬ ሊ ላይ ፤ ከኔዞፈረንጂያል  ካንሰር ሙሉ በሙሉ በማገገም ላይ እያለች ነበር ወንድሟም ካንሰሩ እንዳለበት ያወቀችው   "የሚሆነው ይሆናል ። የሆነ ነገር አንዴ ከተከሰተ በኋላ  ወደኋላ ሄደን እንዳይከሰት ማድረግ አንችልም ። ሁኔታውን  እየተጋፈጥን መንገዳችንን መቀጠል አለብን ። ካንሰሩ በልጄ ላይ እኔ ላይ በደረሰበት መንገድ ቢከሰት ፣ እንዲወገድ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ ”  ትላለች  ስሬ ሊ ስትናገር


ለሚወዱት ነገር የመታገል “ቆራጥነት”
 
Razia-Nasreen-Sultana_Paint.jpg
 
አዕምሮዎ ሲሰቃይ ሰውነትዎ ይሰማዋል ፣ አመኑም አላመኑም ፣ ጭንቀት አካላዊ ምልክቶች አሉት ። ተስፋ አልባ መሆን ሁኔታውን የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል ተብሎ ይታመናል ፣ እንዲሁም በተመሳሳይ በተስፋ መሞላት እና በሕይወት የመኖር ፍላጎት ሁኔታውን በእጅጉ ያሻሽላል ተብሎ ይታመናል ፣ እንደውም በአንዳንድ ሁኔታዎች ለውጡ ሐኪሙ ከሚጠብቀውም በላይ እስከመሆን ድረስ ሊሆን ይችላል ። ለብዙ ሰዎች ይህ የመኖር ፍላጎት ከሌላ ቦታ ሳይሆን ከቤተሰብ ፍቅር የሚመጣ ነው ። ከጡት ካንሰር ህይወታቸው የተረፈው የ 62 ዓመት የሆኑት ባንግላዴሻዊ  ራዚያ ናስሪን ሱልጣና ፣  በህክምናቸው ወቅት አንድ ዓላማ ብቻ ነበራቸው - ቤተሰቦቻቸውን እንደገና ማየት ። "ምንም እንኳን በኬሞቴራፒ እራስ ምታቱ ፣ ማቅለሽለሹ ፣ ምግብ ሆድ ውስጥ መቀመጥ አለመቻሉ የሚያሰቃይ ቢሆንም ፣ ጉዞዬን እንድቀጥል ያደርገኝ አንድ ነገር አለ ፤ ወደ ልጄ መመለስ መቻል እና የልጅ ልጄን ማየት መቻል ፡፡ በሕይወቴ ውስጥ ሁሉም ነገሬ ናቸው ፡፡ በሕክምናው ሥቃይ መጽናት የቻልኩበት ምክንያት እነሱ ናቸው" ይላሉ ወ / ሮ ራዚያ


ለሌሎች ያለን ፍቅር የመኖር ፍላጎትን የሚያጠናክር ቢሆንም እኛ ለራሳችን ያለን ፍቅር ካንሰርን እንድንቋቋምም ያነሳሳናል ፡፡ መዝፈን የሚውዱት  እና በሪል እስቴት ስራ ላይ የተሰማሩት ቪዬትናሚያዊቷ የ 53 ዓመት ሴት ወ/ት ንጉየን ቲ ማን እንደተናገሩት  “ዕጢዎቹ በማንኛውም መንገድ ከተረበሹ ወዲያውኑ በሰውነቴ ሁሉ ውስጥ  እንደሚሰራጩ ሰምቼ ስለነበረ በሕክምና ላይ አፋጣኝ ውሳኔ ከማድረግ ተቆጥቤ ነበር ፡፡ ሆኖም እናቴ በካንሰር ምክያኛት በሞት በተለየችኝ ጊዜ እኔ የምንከባከብው ቤተሰብ ስላለኝ እንደ እርሷ  ሌላ የካንሰር ሰለባ መሆን እንደሌለብኝ ወሰንኩ ፡፡ ሌላው ማጣት የማልፈልገው ነገር የመዝፈን ችሎታዬን  ነው ምክንያቱም ዘፈን የህይወቴ እውነተኛ ፍቅር ነው ፡፡ በዘፈን ውድድሮች ላይ እንኳን ሳይቀር ሽልማቶችን አግኝቻለሁ ። ለመዝፈን ወደ መድረክ በወጣሁ ቁጥር በጣም ደስ ይለኛል ከጓደኞቼ ጋርም ጥሩ ጊዜ አሳልፋለሁ ። ” የሚሉት  ወ/ት ቲ ማን አሁን ከካንሰር ነፃ ሆነው የክልል የዘፈንን ውድድር በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ ፡፡


ከላይ እንደተጠቀሰው የሰውነት ሥነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ንዑስ ክፍሎች በጣም የተሳሰሩ ናቸው ፡፡ በተለይም ከበሽታ ጋር በምንታገልበት ጊዜ በማዕበሉ ውስጥ ሰውነት በድፍረት እንዲያልፍ አዕምሮን ማጠንከር ያስፈልጋል ፡፡ በዚህ ዓመት በአለም የካንሰር ቀን የሆራይዘን ካንሰር ማዕከል የካንሰር ህሙማንን ለመንከባከብ እና “ ነኝ እናም እሆናለሁ” ከሚለው መሪ ቃል ጋር በተያያዘ  ፅናትን በማጠናከር  ላይ እንደምንሳተፍ እናሳውቃለን ፡፡ ተስፋ ከፅናት ጋር በመሆን ከሌሎች ጋር የማይመሳሰል ኃይል አለው
 
For more information please contact:

Related Packages

Related Health Blogs