bih.button.backtotop.text

በግማሽ ተዛማጅ የመቅኔ ህዋስ ንቅለ ተክላ(ዝውውር)፡ እጥፍ ድርብ ተስፋ፣ ቆይታን በግማሽ የሚቀንስ፣ ሙሉ በሙሉ የሚያድን

የ ሀፕሎአይደንቲካል (haploidentical) የመቅኔ ህዋስ ንቅለ ተከላ/ዝውውር (በተለዋጭ መጠሪያው በግማሽ ተዛማጅ ንቅለ ተከላ/ዝውውር) በሆራይዘን ክልላዊ የካንሰር ማዕከል ውስጥ በጣም ውጤታማ የሕክምና አማራጭ ነው ፡፡ የደም እና የካንሰር ስፔሻሊስት የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር ኮረኔል ዶ/ር ዊችያን ሞንኮንሲትራጎን ሲገልፁ “ለደም ካንሰር ሕክምና የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ አንዱ የህክምና አማራጭ ነው ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ከካንሰር ሙሉ በሙሉ የመዳኛ ብቸኛ ተስፋ ነው ፤  ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የተዛመደ ወይም ከታካሚው ጋር የሚጣጣም የአጥንት መቅኔ ያለው ለጋሽ የማግኘት እድሉ በጣም ጠባብ ነው፡፡ ሆኖም በአሁን ወቅት 50% ተዛማጅ መሆኑ ብቻ ከፍተኛ የመሳካት እድል ያለው ህክምና ለማድረግ በቂ ነው፡፡” ብለዋል

“የደም በሽታዎች ላለበት ታካሚ፣ ከኬሞቴራፒ (chemotherapy) እና ከፋርማኮቴራፒ (pharmacotherapy) ህክምናዎች ውጪ ፣ ሌላኛው ሙሉ እና ፍፁም የሆነ የመዳኛ ቀሪ አማራጭ ህክምና የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ ብቻ ነው፡፡ ይህ ህክምና ለተለመዱት የደም ካንሰር በሽታዎች ፣ እንደ ሊምፎማ (lymphoma) እና አኪዉት ሊምፎብላስቲክ ሉኪሚያ (acute lymphoblastic leukaemia) ላሉ  እንዲሁም  አፕላስቲክ ደም ማነስን (aplastic anaemia ) ጨምሮ፣ ታላሲሚያ (thalassemia) እና የተወሰኑ ከበሽታ መከላከል ( autoimmune diseases) ጋር ተያይዘው ያሉ የበሽታ አይነቶች ላይ ውጤታማ ነው።” በማለት ዶ/ር ዊችያን ስለ ህክምና አማራጮቹ አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
‘’ለአንድ ታካሚ ትክክለኛውን የበሽታ ሁኔታው ያለበትን ድረጃ  የማሳወቅ ሂደት ብዙውን ጊዜ በታካሚው የግል የእምነት ሥርዓቶች ፣ አስተሳሰቦች እና ሃይማኖቶች ይወሳሰባል ፤ ይህ ደግሞ ባሉት የሕክምና አማራጮች አዋጭነት  ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡ ለምሳሌ ፣ የይህዋ ምስክር የሆኑ ታካሚዎች ደም ልገሳን አይቀበሉም ፡፡ ፍላጎታቸውን በታማኝነት እያከበርን በተቻለን አቅም ሁሉ እነሱን የምናክምበት መንገድ መፈለግ አለብን፡፡ የታካሚዎቻችንን አዕምሯዊ ወይም መንፈሳዊ የህይወት ክፍል ሳያከብሩ አካልን በግድየለሽነት ማከም ለእኛ ስህተት ነው። ” አሁን አሁን የመቅኔ ንቅለ ተከላ  እንደ አጥንት መቅኔ ፣ ደም ወይም የእንግዴ ልጅ  ባሉ የተለያዩ የመቅኔ ህዋስ ምንጮች ሊከናወን ይችላል ፡፡

 

በ50% ተዛማጅነት የ100% ዕድል

የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላን አስቸጋሪ የሚያደርገው ከታካሚው ሂዉመን ሉኮሳይት አንቲጂኖች (human leukocyte antigens) ጋር 100% የሚዛመዱ የመቅኔ ህዋሶችን  ማግኘት ነው ፡፡ ይህን ማግኘት ቀላል አይደለም ፣ ምክንያቱም ወንድሞና እህት እንኳን ሙሉ የሆነ የህዋስ ተዛማጅ የመሆን እድላቸው ከአራት አንድ ብቻ ነው ፡፡ በስጋ የማይዛመዱ ሰዎች 100% የሆነ የህዋስ ተዛማጅ የመሆን ዕድላቸው እጅግ በጣም ጠባብ ነው ፤ ምናልባት ሊገኝ እንኳን ከተቻለ አንድ የህዋስ ተዛማጅ  የሆነ ሰው ለማግኘት በጣም ረጅም ጊዜ ይወስዳል። በዚህም ምክንያት የተነሳ እስከ አሁን ድረስ የሕክምናው ተመራጭነት ውስን ሆኖ ቆይቷል ፡፡ ዛሬ ለህክምናው ሙሉ የሆነ የመዳን አጋጣሚ  50% የመቅኔ  ህዋስ ተዛማጅ መሆን ብቻ በቂ ነው ፡፡

 

ታካሚ የሚተማመንባቸው የባለሙያ ቡድኖች

“አንድን የሕክምና ዕቅድ ከግምት ውስጥ ስናስገባ  ሁል ጊዜ  ለታካሚው ሁኔታ ቀዳሚውን ቦታ በመስጠት ነው። ምርመራን ማደረግ እንዲሁም  ህክምና መስጠት የሚቻልበት የጊዜ ገደብ ለእያንዳንዱ ታካሚ የተለያየ ይሆናል ፡፡ ብዙ ነገሮችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን ፣ ለምሳሌ ለታካሚው ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተወሰነ ጊዜ እንዲያሳልፉ መፍቀድ ፤ ለታካሚው ሞራል በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡ ሆኖም የሕክምናው ቆይታ በተቻለ መጠን የተጠናከረ እና ቀጣይነት ያለው መሆን አለበት። ” ሲሉ ዶ/ር ዊችያን ልዩ የባለሙያ ቡድኑ ነርሶችን ፣ የፋርማሲ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የህክምና ባለሙያዎችን ያካተተ ስለመሆኑ በዝርዝር ተናግረዋል ። “በሁሉም ልዩ  ሞያዎች (specialties) ላይ ያሉ ሐኪሞቻችን ለታካሚው ጥቅም ሲባል እርስ በርስ በእውቀት ይተጋገዛሉ ፡፡ ከላቦራቶሪ ምርመራዎች እስከ ዲያግኖስትክ የምስል ምርምራ  ኤክስ ሬይ (x-ray) ፣ ሲቲ (CT) ፣ ኤም አር አይ (MRI) ፣ ፔት ስካን (PET SCAN) ሁሉንም ማድረግ እንችላለን ፡፡ ታካሚው ለጤንነቱ እና ለህክምና ዕቅዱ ተገቢ የሆነ እጅግ በጣም ጥሩ አመጋገብ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጡ የምግብ ጥናት ባለሙያዎች እንኳን ሳይቀር አለን ፡፡ የአጥንት መቅኔ ታካሚዎች በኢንፌክሽን የመያዝ እና የሰውነት መቆጣት አጋጣሚን ለመቀነስ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ አመጋገብ ያስፈልጋቸዋል ፡፡ ለምሳሌ በሽታ የመከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆነ ታካሚዎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ዳቦው እንኳን ያለ እርሾ መጋገር አለበት

 

እውቀት የመዳኛ ኃይል ነው

ዶ / ር ዊችያን  ታካሚዎቻቸውን ሲያክሙ   “ ታካሚዎችንን እንደ ራሳችን ቤተሰቦች አድርገን ለማከም የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን” የሚለውን እንደ መመሪያ መርህ  አስምረውበት ነው ፡፡ “ አፕላስቲክ የደም ማነስ (aplastic anaemia) እና ዝቅተኛ የደም ሴል ቁጥር የነበረባቸው በአንድ ወቅት የአረብ ታካሚ ኬዝ ነበር ፡፡ በጊዜውም ታካሚው የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ ማድረግ ነበረበት ፡፡ ታካሚው ከአስር በላይ ወንድሞችና እህቶች ቢኖሩትም አንዳቸውም ቢሆኑ ከእርሱ ጋር  የሚዛመድ የአጥንት መቅኔ ህዋስ አልነበራቸውም። ይህም የግማሽ ተዛማጅ ወይም የሃፕሎአይደንቲካል የመቅኔ ህዋስ ንቅለ ተከላ (haploidentical stem cell transplant) እንዲያስፈልጋችው አድርጎት ነበር፡፡ ታካሚውን በሚገባ ለመንከባከብ መላውን የቡድኑን አባላት ማንቀሳቅስ  ነበረብን ፣ በጣም ጥንቃቄ የሚያሻው ሁኔታ ነበር። የነጭ የደም ሴል ቁጥሩ ቀንሶ ፣ መብላት አቅቶት እና ያለማቋረጥ እያስቀመጠው በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የነበረበትን ጊዜ አሳልፈናል ፡፡ በመጨረሻ ግን ስኬታማ ሆነን ድኖ ወደ ቤቱ መመለስ ችሏል ፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሊጎበኘን ሲመጣ ፤ ደስተኛ እንዲሁም ጤናማ ሕይወት እየኖረ መሆኑን እና በቅርቡ ሊያገባ እንደሆነ ነገረን ፡፡ ”

“ለሁሉም የካንሰር ህመምተኞች ተስፋ እንዳይቆርጡ መናገር እፈልጋለሁ ፣ ምክንያቱም በአሁን ጊዜ የካንሰር ህክምና ከቀድሞ በእጥፍ ድርብ ተሻሽሏል ፣ በተለይ ደሞ ለደም ካንሰር ህክምና፡፡ ልንጠቅምባቸው የምንችላቸው በጣም ብዙ መድሃኒቶች እና የሕክምና ዘዴዎች አሉ። ስለዚህ በትክክለኛው ህክምና ሙሉ ለሙሉ የሚያገግሙበት አጋጣሚ እያለ  ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም ፡፡ “ በማለት ዶ/ር ዊቺያን ንግግራቸውን አጠቃለዋል ፡፡”

 
For more information please contact:

Related Packages

Related Health Blogs