bih.button.backtotop.text

የነረስ አሳሽ፡- ለካንሰር ህሙማን የጓደኛ የምክር እና የድጋፍ አገልግሎት

“ተመርምሮ የካንሰር በሽተኛ ሆኖ መገኘት በህይወት ውስጥ እጅግ በጣም ከፍተኛ ስሜት የሚፈጥር ሲሆን በዚህ በሽታ የተጠቁ ህሙማን ከምንም በላይ ተመርምሮ የካንሰር በሽተኛ መሆናቸውን ካወቁ ከምንም ተስፋ የሚቆርጡና ከባድ ህይወት እንደሚሆንባቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ለህሙማን አስፈላጊ እና ተገቢ እገዛ ማድረግ ከሁኔታው ጋር ስምምነት ለይ እስከሚደረስ ድረስ ተገቢ እንክብካቤና ድጋፍ መስጠት ዋና ተግባሬ ነው፡፡”
 
nurse-navigator.jpg

- ኬ. ናታሱክታ (ማም) በቡራንግራድ ሆስፒታል ባንክ ኮንግ የሆሪዞን ካንሰር ማዕከል ከፍተኛ ሚና እገዛ የሚያደርጉ ነርስ ናቸው፡፡

ለነርስ አሳሾች በየጊዜው ከባድ ፈተና የሚሆንባቸው ስለዕለት ተዕለት የሚያደርጉት የህክምና አገልግሎት ሲሆን በወቅቱም በተለያዩ መንገድ ለካንሰር ህሙማን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በነርስ አሳሽነት ሚና ኬ.ማም 13 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው ሲሆን በሁሉም የአገልግሎት መምሪያዎች ለህሙማሙ ተገቢ ህክምና እና የተቀናጀ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን በማረጋገጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን በመሆኑም ህሙማን እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ የህክምና እክብካቤ አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ በየቀኑ መነሻ ለእያንዳንዱ ህሙማን የላቀ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ትኩረት እና ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ውሳኔ አረገዋለሁ፡፡ በእያንዳንዱ የሥራ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ፈተናዎች እንደሚያጋጥሙኝ ይታወቀል፡፡ ሆኖም ግን ጉዳዩ ምን ያህል ውስብስብ ቢሆንም ተገቢ አገልግሎት ለመስጠት ለራሴ ቃል በመግባት አስፈላጊውን እንቅስቃሴ በየቀኑ እጀምራለሁ፡፡ በየጊዜው እያንዳንዱ ህሙማን አግባብነት ያለውን ህክምና በምሰጥበት ጊዜ ከፍተኛ እርካታ ይሰማኛል፡፡ ህሙማኑን መርዳት ሁሌም በየቀኑ የሚያነሳሳኝ አሰራር ነው፡፡

የአሳሽ ነርስ አብይ ሚና​

የአሳሽ ነርሶች አብይ ሚናዎች እንደ ኬ.ማም በመጀመሪያ እይታ ቀላል መስሎ ሊታይ ይችላል፡- በአጠቃለይ የተቀናጀ ስራ ለማከናወን በርካታ ግንኙነቶች የሚያስፈልግ ነው፡፡ በርግጥ ለሆራይዞን የካንሰር ህሙማን ማዕከል የነርሶች ዋንኛ እና አብይ ሚናዎች አስፈላጊ እንክብካቤዎች በተገቢው ሁኔታ መስጠት ነው፡፡ በብዙ ሁኔታዎች አዳዲስ ህሙማን ወደ ሆራይዞን ሆስፒታል የሚመጡት በከፍተኛ ደረጃ በህመሙ የተሰቃዩ እና ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ከፍተኛ አቅም አንሷቸው ነው፡፡ እንዲሁም የወደፊት ተስፋቸውን ምንም የማያውቁ ተስፋ የቆረጡ መስለው ይመጣሉ፡፡ ኬ.ማምስ የመጀመሪያ አብይ ሚና ለህሙማን ከፍተኛ እና አስፈላጊ እገዛ በሚያስፈልግባቸው ጊዜ ደርሳላቸዋለች፡፡

“ከ60 በመቶ በለይ የሚሆኑ የካንሰር ህክምና ያገኙ ታካሚዎች በተወሰነ መጠን የአዕምሮ ህመም የሚያጋጥማቸው ሲሆን ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አልፎ አልፎ ማወቅ ሲሳናቸው ይስተዋላሉ፡፡ ኬ.ማም እንደሚያብራሩት ህመምተኛውን ካገኙ በኋላ ከታካሚው የተሻለ እንክብካቤ ማግኘቱን ማረጋገጥ እና ለአካላዊም ሆነ አዕምሮአዊ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት እሰጣለሁ፡፡ በአብዛኞቹ ሁኔታዎች ህመምተኞችን ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡ ታካሚው የሚቀበላቸው የህክምና እርዳታዎች ፍጹም የሆኑ እና አዕምሮአዊና አካላዊ ብሎም መንፈሳዊ ጎንን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ በአካላዊ ደረጃ ፈጣን እና ግልጽ የሆነ ቅንጅት እንዲኖር የተቻለንን እናደርጋለን ለምሳሌ ታካሚው የጨረር/ኪሚዮቴራፒ በሚፈልግበት ጊዜ ከሚመለከተው ዲፓርትመንት ጋር በመገናኘት ወይም ታካሚው የተወሰኑ ምግቦችን ለመብላት ሳይችል ሲቀር የስነ ምግብ ባለሙያዎችን በመገናኘት ምክር የምንጠይቅ እና የተቀናጀ ስራ የምንሰራ ይሆናል፡፡ የትኛውን አካል ማግኘት እንዳለብን መለየታችን እርዳታውን በተሻለ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመስጠት እና አፋጣኝ መፍትሄ ታካሚው እንዲያገኝ ለማድረግ እጅጉ ጠቀሜታ አለው፡፡”

አዕምሮአዊ ክፍሎች አስፈላጊታቸው የዚያን ያህል ነው ታካሚዎች የስሜት እና የዝንባሌ ብሎም የባህሪ እርዳታ እንዲያገኙ ማስቻል ወሳኝ ነው፡፡ ዋና ሚናው ከታካሚው ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት በመፍጠር ምክር ለመስጠት እና ታማሚው ዘና እንዲል ብሎም ድጋፍ እንዲያገኝ ማስቻል ነው፡፡ በመጨረሻ የምንሰጠው መንፈሳዊ እርዳታ የዚያን ያህል በእጀጉ ጠቀሚታ ያለው ሲሆን ህመምተኛው የሙስሊም ሃይማኖት ተከታይ ከሆነ በእያንዳንዱ ቀን የጸሎት ስነ ስርዓቱን እንዲያከናውን ይረዳል፡፡ የእያንዳንዱን ህመምተኛ የዘወትር የአኗኗር ዘይቤ መረዳት ያስፈልገናል፡፡

በአማራጭነት ለሚቀርብ የህክምና እርዳታ የህሙማን አያያዝ

ሌላው የህክምና እርዳታ/ነርስ ናቪገተር ጠቃሚ ተግባራት የሆስፒታሉን የውስጥ ዲፓርትመንቶች ቅንጅት መያዝ እና ከሚመለከታቸው የውጪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት መፍጠር ነው፡፡ ይህ በርካታ የሙያ ዘርፍ ያላቸውን የቱዩመር/የካንሰር እጢ ቦርድ በተቀናጀ ሁኔታ ማሳደድ እና ይህንኑ ተግባር በእያንዳንዱ እሮብ ቀን በማከናወን ዶክተሮች መፍትሄዎቻቸውን ዘረፍ ብዙ እንዲያደርጉ ያጋጠማቸውን የህክምና ጉዳይ ለሌሎች ለማጋራት ያስችላቸዋል፡፡ የመንታይ ዲስፕለነር ቱመር ቦርድ ቡድን ከተለያየት የህክምና ዘርፍ የመጡ ለምሳሌ ከዳይኖስቲክ ሪዲዮሎጂስት ከነርሶች እና ከሌሎች የህክምና ዘርፎች የተወጣጡ ቢያንስ 30 ባለሙያዎችን ይይዛል፡፡ ታካሚው ከላብ ሞሎኪዮላር ሲንጋፑር ወይም ዩኤስ ባዩክሲ የህክምና እርዳታ በሚፈልጉበት ወቅት ኬማምስ ቁልፍ የሆኑ አጋዥ ድርጅቶችን በማቀናጀት ተሳትፎና በተለዩ ጉዳዮች ላይ ስብሰባ እንዲያካሂዱ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡

የቡድን ስራና ችግሮች በአፋጣኝ መፍትሄ መስጠት​

በሆራይዘን የካንሰር ማዕከል ያለውን የላቀ ጠቀሜታ የሚሰጥ ሚና ምን እንደሆነ ብጠይቅ ምላሼ የሚሆነው እያንዳንዱ የሥራ ሚና እኩል ጠቀሜታ እንዳለው ነው፡፡ በሆራይዘን ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ለህሙማን ነው፡፡ በዚህ ማዕከል ውስጥ በአንድ እንድተቀናጀ ነጠላ ቡድን ሆነን የሥራ ሃላፊነታችንን እንወጣለን ለምሳሌ ታካሚው የውጪ ሀገር ዜጋ በሚሆንበት ጊዜ ይህንኑ የቡድን ስራችንን እናከናውናለን፡፡ በሁሉም አይነት ሁኔታዎች ከታካሚው ጋር የመልዕክት ልውውጥ ለማድረግ እንዲረዳን የትርጉም ባለሙያዎችን ለዚሁ ስራ እንጋብዛለን፡፡ የተመደበው ዶክተር የቀረበለትን ፊልም በሚመለከትበት ወቅት ወዲያውኑ በተጨማሪ ምክክር ከኪሚዮቴራፒ ባለሙያ ጋር ግንኙነት ለማድረግ እንወስናለን፡፡ የኬሚዩቴራፒ ባለሙያው እንደመጣ ታካሚው የጨረር ወይም ራዲየሽን ህክምና እርዳታ ያስፈልገው እንደሆነ ከስምምነት ላይ ይደረሳል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ጉዳዩን በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ሪዲዮሎጂስት ለዚሁ ተግባር እንጋብዛለን በመጨረሻም የህክምና ሂደቱ የቀዶ ህክምና ዶክተር የሚያሳትፍ ሲሆን ከዚህ የህክምና ሂደት በኋላ በአፋጣኝ ከቀዶ ህክምና ዶክተር ጋር ውይይት እናደርጋለን፡፡ ይህ በምን አይነት እና በተቀናጀ መልኩ ስራችንን እንድናከናውን ማሳያ መሆኑ አኳያ ከመኖሪያ ሀገራቸው ርቀው የመጡ ታካሚዎች ወይም ሰዎች ሆስፒታሉ አካባቢያቸው እዳለ ሆስፒታል ሆኖ እንዲሰማቸው በቅልጥፍና ስራችን እና ከናውናለን፡፡

ክብረ በዓልን ጨምሮ ስራችንን በመስራት ስለምናገኘው ደስታና ቁርጠኝነት​

ታካሚው በመጀመሪያ አምኖበት አእምሮው እንዲወስን ከተደረገ በሃላ እንደ ኬ.ማም እምነት ስራዋ የአንደ የሥራ ሂደት አገልግሎት ነው፡፡ ይህም በክብረ በዕላትም ቢሆን የሚከናወን ነው፡፡ ድንገተኛ ታካሚ ሊያጋጥም ይችላላ ከሚል እሳቤ ሁል ጊዜም በባዕላት ያላትን የጊዜ አጠቃቀም ክፍት ታደርጋለች፡፡ አልፎ አልፎ በባዕል አከባበር ላይ ውሳኔ ሊያስወስን የሚችል የስልክ ጥሪ ያጋጥመኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ሁሉንም ሁኔታዎች ለማመቻቸን እና ለማቀናጀት ዝግጁና ደስተኛ ነኝ፡፡ አንድ ጊዜ ታካሚ ደም እያስመለሰው መጣበት ጊዜ ነበር፡፡ በስራ ላይ የነበረችው ነርስ ሁኔታውን ከመረመርች በኋላ በታካሚው ላይ ያየችው ምልክት ከባድ እንደሆነ ለማስተዋል በመቻሏ ነርሷ እኔን ለመጥራት ወሰነች እኔም ለድንገተኛ ታካሚው ዶ/ር በመመደብ እና ድንገተኛ ክፍል በማመቻቸት አስቸኳይ የህክምና እርዳት እንዲያገኝ አድርጊያለሁ፡ ምክንያቱም ታካሚው የነበረበት ሁኔታ ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚችል እና ምን አልባትም እስከ ሞት የሚያደረስ ስለነበረ ነው፡፡ ሆኖም ግን ታካሚው አፋጣኝ ትኩረት እና የህክምና እርዳታ አግኝቶ ከህመሙ ሊያገግም ችሏል፡፡ የታካሚውን ህይወት ለመታደግ በአበረከትኩት አስተዋፆ እኔም የላቀ ደስታ ይሰማኛል፡፡ ጥረታችን መልካም ዜናን ይዞ እስከመጣ ድረስ በሚሰማን ድካም ያን ያህልም አይከፋንም፡፡

ለዝርዝሮች ትኩርት መስጠት ቁልፍ ተግባር ነው፡፡

አንዳንድ ህሙማን ለአማራጭ መድሃኒት ወይም ሌላ የተፈጥሮ የህክምና እርዳታን ይመርጣሉ፡፡ ይህም ተግባር የህክምና እርዳታ ሰጪ ቡድኑ ሳያውቅ በግላቸው የሚያከናውኑት ተግባር ነው፡፡ ውጤታቸውንም በምናይበት ጊዜ የሚጠበቀው ውጤት እና ከትክክለኛው የህክምና እርዳታ የሚገኘው ውጤት ከትክክለኛ የዚህ ህክምና ውጤት ጋር ተመሳሳይ እንደማይሆን እርግጠኛ ነን በአብዛኛው ህሙማን በቀጥታ ሀሳባቸውን ስለማይገልፁ ለታካዎች ስንል ከህሙማኖች ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት መገንባታቸው በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ ታካሚዎች ጤናቸውን ለመጠበቅ እና በአስቸጋሪ የጤና ጊዜና መሰናክል ወቅት ምችቶ እንዲሰማቸው ከእኛ ጋር መተማመንን ቢገነቡ በእጅጉ ጥቅም ይኖረዋል አልፎ አልፎ ላልተረጋገጡ የባህል መድሃኒቶችን ወይም የነጭ ደም ሴላቸውን ብዛት የሚቀንሱ እና ጉበታቸውን ሊጎዳ የሚችል ደጋፊ መድሃኒቶችን ህሙማን ይወስዳሉ፡፡ አንዳንድ ህሙማን ሆን ብለው ያለበቂ እውቀት እና ሁኔታው ስለሚያስከትለው ውጤት ግንዛቤ ሳይኖራቸው የካናቪስ ዘይትን ይወስዳሉ፡፡ ሆኖም ግን አንደ ጊዜ የበሽታውን ሁኔታ በተመለከ ሙሉ ግንዛቤና ምክር ካገኘ ቡድኑ ህመምተኛውን የሚጠቅም መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል እርዳታ ያቀርባል፡፡

ህመምተኛውን እንደ ኬ.ማም የቤተሰብ አባል እርዳታ መስጠጥ እንዳለን እናምናለን የጤና እክል ሲያጋጥማቸው ህሙማን ጭንቀት ላይ ይወድቃሉ እንደሁም በእንደዚህ አይነት አስቸጋሪ ወቅት ሊመኩበት የሚችሉ እርዳታ የሚሰጣቸውን አካል ይሻሉ፡፡ ሰለሆነም ስራችን በተቻለ አቅማችን ማከናወን እና ውድና ወቅታዊ የሆነ የህክምና እርዳታ መኖሩን ለማረጋገጥ ከሁሉም ተጓዳኘ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አለበት፡፡

ለነርስ ናቪገቴር የሥራ ተግባራት ምሶሶ የሚሆኑ ስነምግባሮች​

እያንዳዱን ቀን ከእንቅልፍ በምነቃበት ወቅት የተቀረው የቀኑ ክፍለ ጊዜ ፈተና የሚበዛበት እንደሆነ አስባለሁ ስለሆነም በቡድናችን ውስጥ የሚደረሱት ሁኔታዎች ላይ መፍትሄ ለመስጠጥ ከቡድኑ ቀድሜ የመፍትሄ ሀሳብ ላይ አተኩራለሁ በዕለቱ መጨረሻ በቀኑ የተከናወነውን እያንዳንዱ ተግባር ወደ ኋላ ተመልሼ በመቃኘት ሁኔታዎች ወደ ፊት በምን አይነት መልኩ መሻሻል እንዳለባቸው አስባለሁ፡፡ በእውነት የምትጠይቁኝ ከሆነ የነርስ ናቪጌተር ስራ በእጅጉ አድካሚ ነው፡፡ ይህንን አልክድም ነገር ግን ሁኔታዎች ወደ ኋላ መለስ ብዬ ስመለከት እና ቡድናችን እንዴት የታካሚዎች የጤና ሁኔታ ለማሻሸል ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ እመለከታለሁ፡፡ እንዲሁም ቡድኑ የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ የሚያደርገውን ጥረት ሳስብ ድካሜ ቀልጦ ይጠፋል፡፡
 
For more information please contact:

Related Health Blogs