bih.button.backtotop.text

የልብ ኃይል፡- በኦንኮሎጂ ነርሶቻችን የሚሰጡ የማቀፍ እና የሰላምታ አሰጣጦች

‹‹ለካንሰር በሽታ ህሙማኖች የህክምና እንክብካቤ በምናደርግላቸው ወቅት ከምንም በላይ እጅግ ከባድ ነገርለኬሞቴራፒ /ለኬሚካል ህክምና የደም ስሮች ማግኘት ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ በርካቶች አብዛኛው ጊዜበጣም በርካታ በመርፌ የሚሰጡ ህክምናዎች እና በእንክብል መልክ የሚሰጡ በርካታ መድኃኒቶችንሲከታተሉ ቆይተው ወደ ማእከሉ ስለሚመጡ ለህክምና ያልተጋለጡ የደም ስሮቻቸው ከሚፈለገው ደረጃበታች ጥቂት ስለሚሆን እና በመካከላቸው ያልተፈለገ ርቀት ክፍተት ስለሚያስከትል ነው፡፡ ይህ በመሆኑምክንያትም ሀኪሞቻችን ህክምናው ለመስጠት የሚያስችሉ ማእከላዊ መስመሮች እንደ አማራጭ ለይተውእንዲያቀርቡ እናደርጋለን፡፡ በዚህ አይነትም የታማማዎቹን የህመም ስቃይ መቀነስ ይቻላል፡፡›› ይህ አሰራርም የሆራይዘን የካንሰር ሕክምና ማእከል የኦንኮሎጂ ነርሶች ስራ አስኪያጅ የሆነችው ካኒካ ቡንፕራቾም በህክምና አገልግሎቱ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማዳን ከቀረቡት የመቋቋም አቅም የማዳበር ስልቶች መለስተኛው ምሳሌ ነው፡፡
 
የኦንኮሎጂ ነርስ መሆን ማለት የካንሰር ህሙማን የበሽታውን ህክምና አገልግሎት በሚከታተሉበት ሂደት ሁሉከየትኛውም የህክምናው ባለሙያ በላይ ከበሽታው ታካሚ ህሙማን ጋር ጥልቅ ግንኙነት ያላቸው መሆንነው፡፡ በሽታውን የማከሙ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ እና መረጃ የሚያስፈልግም ሆነ፤ ስላጋጠማቸው በሽታአስመልክቶ መረጃ እና ማብራሪያ የሚያስፈልግ ከሆነ፤ ወይም በድህረ ህክምና ወቅት ለሚደረግላቸውክትትል አስመልክተው ከየትኛውም የህክምና ባለሙያ ወይም ሀኪም በላይ ቀረበ ግንኙነት የሚያደርጉትየኦንኮሎጂ ነርሶች ናቸው፡፡
 
‹‹ በማንኛውም ሆስፒታል በተቀመጡት መሰረታዊ መስፈርቶች መሰረት በሆስፒታላችን ለሚታከሙታካሚዎቻችን ደህንነት እና ምቾት የሚያስጠብቁ ሁሉ መሟላታቸውን እናረጋግጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህምበላይ በላቀ ሁኔታ ለመልካም ህክምና አገልግሎት እና ሰብአዊ አያያዝ ረገድ ከየትኛውም የህክምና ተቋምበበለጠ የላቀ ልባዊ ሕክምና አገልግሎት መስጠት ቀዳሚ የስራችን መርሆዎች ናቸው፡፡ በዚህ ረገድምነርሶቻችን ለታካሚዎቻቸው መተግበር እንዲችሉ አድርገናል፡፡››  በማለት ካኒካ ታስረዳለች፡፡ ‹‹ በማንኛውም ጊዜለታካሚዎቻችን የምናሳያቸው ቅርበት ለታካሚዎቻችን የተሻለ የሞራል ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ደግሞያለምንም ጥያቄ ወደ የተሻለ የህክምና አሰጣጥ ውጤት ያመራናል፡፡ ››


ጥሩ ክትትል ማድረግ ለታካሚዎቻችን ምናደርጋቸው የልምድ ክህሎቶች  አንዱ ነው
 
‹‹በሕክምና ላይ የሚገኙ እና በሕክምናው በካንሰር ነፃ መሆናቸው ያልተረጋገጠ ታካሚዎቻችን አብዛኛው ጊዜየተረበሸ ስሜት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በህክምናው አገልግሎት አማካኝነት ፈፅሞ ከካንሰር በሽታየማይፈወሱ እንደሆነ እና ምናልባትም በሽታው እንደገና ሊያገረሽባቸው የሚደርግ ስህተት እንደሰሩ ሊያስቡይችላሉ፡፡ ለዚህም ደግሞ ሌላ ተጨማሪ የሚከታተል ሰው እንዲኖር እና መልካም ምክር ለመስጠት ዝግጁ የሆኑትንእናቀርብላቸዋለን፡፡ ለምሳሌ፡ ህመሙ በህክምናው ወቅት እየጠናበት የሄደ ታካሚ ካጋጠመ በመጀመሪ ቀንህክምናውን የጀመረበትን በመጥቀስ እና እንደመነሻ ነጥብ በመያዝ የተሰጠውን ወይም በወቅቱ የታዘዘለትንየህክምና ዓይነት ጭምር እንደገና እንፈትሻለን፡፡ በዚህ አሰራራችን መሰረትም በአፋጣኝ ለጉዳዩ ትኩረትሰጥተን ለሐኪሞች የምንገልፅሲሆን ወይም ደግሞየመድሃኒት ባለሙያዎች  መሰረት ለታካሚው እንዲብራራ እና በአግባቡ እንዲስረዳ እናደርጋለን፡፡>> በማለት ካኒካ ታብራራለች፡፡<< እንዲሁም ታካሚው የቀረበለትን ተመግቦ ካልጨረሰ ወዲያው የስነ-ምግብ ባለሙያ ከታካሚው አንፃር ተስማሚ የሆነ ምግብ መርምሮ እንዲወሰንለት እናደርጋለን፡፡ በዚህ ረገድም ስነ-ምግባር ባለሙያው ታካሚዎች ተመግበው ሰውነታቸውን ጥንካሬ የሚያስቀጥሉበት በህክምናው ሂደት ሁሉ በመልካም መንፈስ የሚመገቡ ወይም ያለምንም ችግር መመገብ የሚችሉበት ሁኔታ ለማመቻቸት ይረዳል፡፡››
የካንሰር በሽታ ሕክምና ተፈጥሯዊ ባህሪ ማለት የኦንኮሎጂ ነርሶች በአግባቡ እና ወጥ በሆነ በተለያዩስነ-ምግባሮች እና ህዝብ ልማዶች የተካኑ መሆን ገባል፡፡ ‹‹ከማንኛው ሁኔታ በህክምና ሂደቱ ውስብስብ እናፈታኝ ሁኔታዎች ሲጋጥሙን የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ በማድረግ በሁኔታዎቹ ላይ በጋራ እንወያይበታለን፡፡በዚህ ኣካሄዳችንም ደግሞ በተለየ የበሽታው ተጠቂ ወይም ታካሚዎች የስነ ልቦና እና መንፈሳቸውንየሚያጠናክሩ ወይም ለማጠናከር በሚረዱ የተለያዩ ስልቶች ሊከሰቱ ስለሚችሉ ጉዳዮች በተሻለ መልኩ ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እንድንችል በውይይት መድረኩ ከእርስ በርሳችን እንማማራለን፡፡ ሁሉም የኦንኮሎጂነርሶቻችን ታካሚዎቻቸውን በእኩል ስሜት መርዳት እንዲችሉ የተለያዩ ቴክኒኮችን በምናካሂደው የውይይትመድረክ እንጋራለን፡፡
 
በተጨማሪም ካኒካ በኦንኮሎጂ ነርሶች ስራ ውስጥ ጠለቅ ብሎ በመግባት የህክምናው አገልግሎት አሰጣጥሂደቶች በኬሞቴራፒ ወይም በኬሚካል ሕክምና ስልት በመጠቀም ዝቅተኛ የደም መጠን ላጋጠማቸውታካሚዎች ወይም ህሙማን የተለያዩ የደም ህዋሳት አይነቶች እና ነጭ የደም ህዋሳት እንደ ፕላዝማ ስርጭትአገልግሎት አሰጣጥ አያያዝ ላይ ትኩረት በማድረግ ተገቢ እና የተፈለገ አገልግሎት መስጠት እንዲቻልአስፈላጊ የነርሶቹን ክህሎቶቻችን ያዳብራል ትላለች፡፡ ‹‹የደም ህዋሳት እና የደም መስመሮች የመለየት ክህሎቶችየተጋነኑ ክህሎቶች ተደርገው አይወሰዱም፡፡ ህሙማኑ በተደጋጋሚ አንድ ዓይነት ወይም ሌላ አይነትመርፌዎች በመውሰድ የደም መስመሮቻቸው እንዲኮማተር ወይም እንዲጠብ ይደረጋል፡፡ ሌሎች የተቀሩየደም መስመሮች ለይተው ማግኘት ትክክለኛ ተጨባጭ የሆኑ ክህሎቶች የሚስፈልግ ሲሆን እነዚህምአንዳንድ ጊዜ እንደ የመለያ መሳሪያ tourniquets ወይም የማሞቂ ጫና እገዛዎች ሊስፈልጋቸው ይችላል፡፡ አስቸጋሪ እናየተወሳሰበ ሁኔታወች ሲያጋጥሙም በዓነቱ ልዩ የሆነ ቁርጠኛ የሆስፒታሉ IV ቡድን የግድ እንዲጠራይደረጋል፡፡››

 
ህመሙን ለማቅለል እገዛ መስጠት እንፈልጋለን

1-1200x800.jpg

‹‹አብዛኛውን ጊዜ ታካሚዎቻችን በህመሙ ሲሰቃዩ እናያለን፤ ለምሳሌ የታካሚዎቻችን ጥሩ የሆነ የደም ስርለህክምናው ለማግኘት ስንሞከር ታካሚዎቻችን ብቻ ሳይሆን ሂደቱ የሚስከትለውን ህመም እኛም እንጋራለን፡፡በእርግጥ ሂደቱ በተወሰነ ጊዜ አንድ ጊዜ ብቻ ቢደረግ የሚመረጥ ቢሆንም ግን ለካንሰር ታካመዊች ግን የግድበተደጋጋሚ መደረግ እንደሚያስፈልግ ይነገራል፡፡›› በማለት ካኒካ  ትገልፃለች፡፡ ‹‹ይህም ብቻ ሳይሆን የህክምናዎቹአሰታጥም ከበድ የሚል ሲሆን ተገቢውን የተፈለገውን የደም ስር ካላገኘ በዙሪያው የሚገኙትን ሌሎችህዋሳቶችን፣ ጡንቻዎችን እና ሌሎች አካላት መግደል ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም ለህክምናው የሚያስፈልጉአማካኝ ወይም ማእከላዊ መስመሮች በምርመራ ሂደት ለይተው እንዲያገኙልን የሐኪሞችን ትብብርእንፈልጋለን፡፡›› እንዲሁም ማእከላዊ መስመር ማስገባት ማእከላዊ/ሴንትራል ቬኑስ ካተተር (ሲቪሲ) ተብሎየሚታወቅ ሲሆነ ይህም በእያንዳንዱ የህክምናው መስጫ ወቅት ደም ስር እንይረበሽ እና እንዳበጣጠስየመከላከል መንገድ ሲሆን በየጊዜው ህክምና መስጠት አለበት፡፡ በተጨማሪም በተለየ የማእከላዊ መስመር
ማነጣጠር የበለጠ ቀጥተኛ ነው፡፡ ‹‹ይህ ማእከላዊ መስመር በሚገጠምበት ጊዜ ሁሉም ነርሶች ሕክምናውንበአግባቡ መስጠት አለባቸው ወይም ደግሞ የታካሚውን ደም ለመቅዳት መርፌውን በታካሚው ሰውነትውስጥ ከማስገባት ይልቅ በቱቦው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድም ታካሚዎቹ በጭራሻ መርፌውበሚያስከትለው ህመም አይጋለጡም፡፡ በዚህ ረገድ በጣም ጥሩ አሰራር የምንከተል ሲሆን ምንም አይነት ጫፍያለው አንዲት ነጠላ ሹል ቱቦ አንጠቀምም፡፡›› በማለት ካኒካ በኩራት ትናገራለች፡፡
 
ስለወደፊት ተስፋ
‹‹እንደ የነርስ ባለሙያነታችን ለታካሚዎቻችን የምናደርገው ወይም የምንሰጣቸው አገልግሎቶች በሙሉከልባችን ውስጠ ነው፡፡ ለታካሚዎቻችን በየቀኑ ያሉትን ለውጦች የምንነግራቸው ሲሆን ሁሉም ታካሚዎቻችንጠንካራ የመንፈስ ስነ ልቦና እና አወንታዊ ስሜት እንዲኖራቸው በቀዳሚነት እንሰራለን፡፡ በየጊዜውከማንኛውም ታካሚያችን ፈገግታ እንዳይርቅ የምንሰራ ሲሆን ከእና የምንለግሳቸው ፈገግታችንም ጠንካራኃይል እንዲኖራቸው ለታካሚዎች አወንታዊ ግብረ መልስ ይሆናል፡፡ በሞቀ እጃችን ስንጨብጣቸው እናበእቅፋችን ስናስገባቸው በመላ ሰውነታቸው እንዲነቃቁ ይረዳቸዋል፡፡›› በማለት የሆራይዘን የካንሰር ሕክምናማእከል ሁሉንም የማእከሉ የኦንኮሎጂ ነርሶችን በመወከል ካኒካ አብራርታለች፡፡
For more information please contact:

Related Health Blogs