bih.button.backtotop.text

መለወጥን መከታተል፡ ከላብራቶሪ የተወሰዱ ሁኔታዎች ወግ

‹‹በተቻለ ፍጥነት የካንሰርን ለውጥ በትክክል ለመለየት ከፍተኛ የሆነ ጥረቶች እናደርጋለን፡፡ ለታካሚዎቻችን በወቅቱ ትክክለኛ የሆነ ህክምና መድሃኒት ለማግኘት ይሄ ወሳኝ ነው፡፡ እኛ ያሉን ላብራቶሪዎች ተመራጭ እና የቅርብ ጊዜ መሳሪያ ፈጣን ውጤቶች ለማግኘት የሚያስችሉን መኖራቸውን በማረጋገጥ ለውጫዊ ላብራቶሪዎች ናሙና ከመላክ ይልቅ ተመራጭ እናደርጋለን፡፡ እያንዳንዱ ደቂቃ ለካንሰር በሽተኛ ወሳኝነት አለው፡፡›› እነዚህ የዊፓ ፓንሞንታ/ፒኤችዲ የበምሩንግራድ ሆስፒታል ዋና የላብራቶሪ ስራ አስኪያጅ ቃላቶች ናቸው፡፡

የእጢ ጂን ምርመራ ለካንሰር ህክምና በአሁኑ ወቅት አንዱ በጣም ጠቃሚ መሳሪያችን ነው፡፡ ኢላማ የተደረጉ ህክምናዎችን ማለትም የመኖር እድልን በከፍተኛ ደረጃ የሚጨምሩ እና የበሽተኞች ስቃይ በተቻለ መጠን የሚቀንሱ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የበምሩንግራድ ሆስፒታል ላብራቶሪ የብዙ አይነት ካንሰሮች ጠቀሜታ ያላቸው የጂን ለውጦችን በአጠቃላይ ለመለየት አቅሙ ያለው ሲሆን ይህ EGFR, KRAS, NARS, BRAF የሚባሉ ለውጦችን ያካትታል፡፡ ይህ ለሀኪሞች በቤት ውስጥ በፍጥነት ካንሰርን የምርመራ ውጤት የመለየት አቅም እና ለታካሚ በሽተኛ በጣም አመቺ የሆነ የህክምና ዘዴ እንዲለዩ ያስችላል፡፡

‹‹የካንሰር የምርመራ ውጤት ብዙ ጊዜ biopsy ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ይህ በበቂ ሁኔታ ተገቢ ሊመስል ይችላል ሆኖም ለምርመራ ህብረ ህዋስ ናሙና ለማግኘት ከፍተኛ ደረጃ ያለው ቀዶ ህክምና ሊያካትት ይችላል፡፡ በእርግጥም ሁሉም ህመምተኞች በዚህ ህመም ያለበት እና አንዳንዴ በጣም አደገኛ የሆነ ሂደት ውስጥ ማለፍ ላይኖርባቸው ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቀረቡ የህዋስ ናሙናዎች ለአጠቅላይ የምርመራ ውጤት በቂ ላይሆኑ ስለሚችል ሙሉ በሙሉ እንደገና መሰራት ሊኖርበት ይችላል፡፡ የቅርብ ጊዜ የጂን ምርመራ ቴክኖሎጂዎች ሲኖሩ የእኛ ላብራቶሪ ከታካሚ የህዋስ ናሙናዎች ቆርጦ የማውጣት እድልን ውድቅ ያደረግን ሲሆን ታካሚው ባለአስፈላጊ ሁኔታ እንዲሰቃይ አንፈልግም፡፡ "

Senior-1.jpg

ዊፓ የNext-generation sequencing (NGS) ማለታቸው ሲሆን ይህ የደም ናሙናዎች መውሰድ በተጨማሪም የፈሳሽ የባዮፓሲን ተብሎ የሚታወቅ-አንዳንድ ጀነቲክ ለውጦች መመርመር ላይ ይመሰረታል፡፡ ቴክኖሎጂው በጣም ትክክል ከመሆኑም በላይ ከካንሰር ሴሎች የDNA ቁርጥራጮች/የሚሽከረከሩ የእጢ DNA/ በትክክል ሊለይ ይችላል፡፡ የNGS አንዱ ዋነኛ ጠቀሜታ በሽተኛው በጣም አነስተኛ ህመም የሚኖረው ሲሆን ሀኪሞች ከዚህ በፊት ከሚያገኙት መረጃ እኩል ወይም በጣም ጠቃሚ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
‹‹ለታካሚው በጣም ስኬታማ የሆኑ ኢላማ የተደረጉ ህክምናዎችን ለእኛ መለየት ከማስቻሉም በላይ NGS በተጨማሪም ህክምናን ይበልጡን ስኬታማ በሆነ መልኩ እንድንከታተል ያስችላል፡፡ በበሽተኛው ውስጥ የሚቆዩ የሚቀሩ የካንሰር ሴሎች ብዛት ይበልጡን በከፍተኛ መደጋገም ትክክለኛ በሆነ መልኩ ከMRI ወይም PET ስካን ይልቅ  ማግኘት ያስችላል፡፡

‹‹አንድ ጊዜ በዚህ በከፍተኛ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የመጣ ታካሚ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል /ICU/ እንዲገባ ተደረገ አስቸኳይ ህክምና አስፈልጓት ነበር፡፡ ሆኖም የህዋስ ናሙና ለመውሰድ በscalpel ውስጥ ማለፍ አልቻለችም፡፡ ሆኖም የህክምና ቡድኑ ከNGS ፈሳሽ ባዮፓሲ ለማውጣት ቻለ፡፡ የምርመራ ውጤቶቹ ሲመጡ የእጢው ፕሮፋይል ኢላማ የተደረገውን የህክምና መድሃኒት ወዲያውኑ ማግኘት ከተቻለ ጋር አብሮ ሊሄድ ስለቻለ ኦንኮሎጂስቱም ወዲውኑ ማዘዝ ችሏል፡፡ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ የታካሚዋ ሁኔታ ተሻሽሎ ICU መልቀቅ ችላለች፡፡›› ዊፓ ይህንን በኩራት ይገልፃሉ፡፡

‹‹የተለዩ ጂኖችን የመለየት አቅም ያለው analyzer/ተንታኝ ያለን ሲሆን ሙሉ ፓነል ምርመራዎች ከማድረግ የተሻለ ነው፡፡ ይህ በከፍተኛ ደረጃ ውጤቶችን ለመተንተን የሚወስደውን ጊዜ ይቀንሳል፡፡ ከሶስት ቀናት በታች በሆነ ጊዜ የታወቁ ውጤቶች ማግኘት የምንችል ሲሆን ይህ ውጫዊ ላብራቶሪ ብንጠቀም የሚወስደውን ጊዜ ግማሽ ያህል ይሆናል፡፡ ጊዜ ወሳኝ ነው፡፡ ለእኛ የካንሰር ታካሚዎች እያንዳንዱ ደቂቃ ወሳኝነት አለው፡፡››

Senior-2-(2).jpg

‹‹በቅርብ ጊዜ የmicrosatellite instability (MSI) ምርመራ ለእኛ repertoire የጨመርን ሲሆን ለimmunotherapy በሽተኛው ምን ያህል ምላሽ እንደሰጠ ይነግረናል፡፡ የእኛ ቀጣዩ ግብ የእኛን አቅም የተወረሱ የጀነቲክ ለውጦች በውርስ የሚመጡ ካንሰሮች እንደሚፈጥሩ መመርመር ወደ መቻል አቅማችንን ማሳደግ ነው፡፡›› ዊፓ ስለ ላብራቶሪያቸው የወደፊት  ማበልፀጎች እቅዶችን ትዘረዝራለች፡፡ ይህ ባህሪ በተለይ በበምሩንግራንድ የሚሰሩ የጤና ፕሮፌሽናሎች ዋነኛ መለያ ሲሆን የእኛ ታካሚዎች በጣም ተመራጭ ህክምና እንዲገኙ ማድረግ የፕሮፌሽናሎቻችን ኩራት ነው፡፡      
For more information please contact:

Related Packages

Related Health Blogs