bih.button.backtotop.text

የታካሚ አስተባባሪዎች፡ በግንባር ቀደም እንክብካቤ ላይ

<<ሁላችንም እንደምናውቀው ቁጭብሎ መጠበቅ ለብዙ ታካሚዎች እጅግ ከባድ ጉዳይ ነው፡፡ ታካሚዎች ለረጂም ጊዜ ቁጭ ብሎ ከጠበቁ ምናልባትም የመበሳጨት ስሜት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ሆኖም አግባብነት ያለው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ላይሆን ይችላል፡፡ ለዚህም ነው ታማሚዎችን የሰአት ጥበቃን እንዴት ማስተካከል ይቻላል የሚለውን ተቀዳሚ ጉዳይ ማድረጋችን ወሳኝ ነው>> እነዚህ በሆራይዘን የክልል ካንሰር ማዕከል የታካሚዎች ማስተባበር ኦፊሰር የሆነችው የፓኒታ ሱቫናፓፕ ቃላቶች ናቸው፡፡

በሆራይዘን የክልል ካንሰር ህክምና ማዕከል የመታከም ሂደት የሚጀምረው ፓኒታን በማግኘት ነው የእሷ ዋነኛ ስራዋ ታካሚዎችን እንኳን ደህና መጡ ማለትና መርዳት ነው፡፡  << የኔ ስራ በኛ ድርጅት (በህክምና መስጫ ማዕከላችን) ለሚመጡ ታካሚዎች አካላዊ ህክምና ማድረግ ብቻ ሳይሆን ስነ ልቦናዊ ፍላጎታቸውንም እናሟላለን፡፡ ለዚህ እንደምክንያት የሚቀመጠው የመጀመሪያ ቀን መሰተንግዶ ማንኛውም በማዕከላችን ለሚመጡ ደምበኞች ላይ በኛ ህክምና ላይ እምነትና ተስፋ እነዲያድርባቸው ያደርጋል፡፡ ውጤታማ ህክምና ለማግኘት መተማመን ያስፈልጋል ፣ ስለሆነም ከመጀመሪያው አንስቶ የታካሚውን ምቾት ለማሟላት እንፈልጋለን ፡፡ እነሱ የሚፈልጉት ምንም ይሁን ምን ፣ አስተባብረን እና በስኬት ፍላጎታቸውን ለማሟላት እንረዳለን ፡፡>>
 

የተለመደ ስራ ከተጨማሪ የተለየ ሀላፊነት ጋር

 
<<ብዙ ጊዜ የተለየ ህክምና የሚሹና ልዩ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች አሉን ለምሳሌ ያህክል ለረጂም ጊዜ መቀመጥ የሚያዳግታቸው ወይንም ዶክተሩን ለመጠበቅ ቶሎ የመናደድ ልማድ ያላቸው>> በማለት ፓኒታ ታብራራለች በመቀጠልም << እንደዚህ አይነት ታካሚዎችን በአእምሮዬ በመሳል አካላዊ ገፅታቸውን  በአእምሮዬ በመሳል እያንዳንዱን ታካሚ በምን መልኩ መቅረብ እንዳለብኝና ፍላጎታቸውን እንዴት ማሟላት እንደምችል በአእምሮዬ እቅድ አወጣለሁ፡፡>>

በእያንዳንዱ ቀን ከስራ መልስ የታካሚዎችን ቀጣይ ቀጠሮ እከልሳለሁ፤ ምን አይነት ታካሚዎች እንደሆኑ፤ ምርጫቸውን፤ የተለየ የሚፈልጉት ነገር ካለ እገመግማለሁ፡፡ ይሄንን እጅግ አድካሚ ወይስ የሚያበሳጭ ሆኖ አገኘሁት? ብዬ ራሴን ስጠይቅ አዎ አንዳንድ ጊዜ አድካሚ ሆኖ አገኘዋለሁ፡፡ ሆኖም ግን በነዚህ ሁነቶች መቆየት አልፈልግም ምክንያቱም ደንበኞቼን 100% ለማርካት የቻልኩትን ያህክል እሞክራለሁ፡ የታካሚዎችን ፍላጎትም ሆነ የቤተሰቦቻቸውን ፍላጎት እንዲሁም ሁሉን የሚመጣውን ነገር በአንድ ላይ ማስተናገድ ብዙ ነገሮች ከኔ ይጠበቃል፡፡>> የፓኒታ ዋነኛ ሀላፊነት የእያንዳንዱን ታካሚ የእለት ተዕለት በትልቅ ትኩረት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ መከታተል ነው፡፡ እንዲሁም ፓኒታ ችግሮችን ከመፈጠራቸው በፊት ለማስቀረት ትሰራለች፡፡ ለምሳሌ  ግጭቶችን ቅድም ተከተል ማስያዝ እና ታካሚው ጥሩ ቆይታ እንዲኖረው ለማረጋገጥ ሁልጊዜ ለነገሮች መፍትሄ መዘጋጀቱን ማረጋገጥን ይጨምራል፡፡
 

ወኔ የሚጨምር የጊዜ አጠቃቀም

 
ብዙ ጊዜ የታዘብኩት ነገር ቢኖር ታካሚዎች ረጂም ጊዜ በሚጠብቁበት ወቅት ላልተፈለገ ጭንቀትና ወጥረት ያጋለጣቸዋል እንዲሁም በህክምናው ሂደት ውስጥ እንቅፋት ይሆናል፡፡
ለዚህ እንደመፍትሄ የወሰድኩት ለምሳሌ የደም ናሙና የሰጡ ታካሚዎች እዛው ከማስጠበቅ ይልቅ ስልካቸውን በመቀበል ወደሚፈልጉበት እንዲሄዱ በማድረግ ተራቸው ሲደርስ መምጣት ባለባቸው ሰአት እንዲመጡ እደውልላቸዋለሁ፡፡   
 
አንድ የኦንኮሎጂስት ባለሙያ የላብራቶሪ ውጤቱን ካየ እና ካረጋገጠ እና ለኬሞቴራፒ ብቁ መሆናቸውን አውቆ ቀጠሮ ከያዘ ታካሚውን ዶክተር ማየት ሳይጠበቅባቸው ቀጥታ ወደ ህክምና ከፍል እወስዳቸዋለሁ፡፡ እንደዛ ማድረጌ ታካሚው በመጠበቅ የሚያጠፋውን ጊዜ ከመቀነሱ በተጨማሪ ለነሱ የበለጠ የሚመች አካሄድ ነው፡፡ ይህም ምንም እንኳን የህክምናቸው ትንሹ ከፍል ቢሆንም በህክምና ማዕከሉ ላይ ያላቸውን እምነት እና መተማመን በመጨመር ረገድ ትልቅ ሚና አለው፡፡
 
በቀን በአማካይ 80 ታካሚዎች በሚመጡበት ሁኔታ የታካሚዎች አስተባባሪ ቡድን ከተለያዩ ሁኔታዎች ጋር ማስተባበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሄም የተለያዩ ክህሎቶችን ማዳበር፤ ቶሎ አዳዲስ መረጃዎችን የመያዝ ችሎታን እና ለዝርዝሮች ትኩረት መስጠትን ያጠቃልላል፡፡ <<ይሄንን ሀላፊነት እንደተቀበልኩ ለራሴ የምችለውን ያህክል ሁሉ ማድረግ እንዳለብኝ ነገርኩ፡፡ የተለያዩ አዳዲስ ክህሎቶችን መማር መቀጠል እንዳለብኝ እና እውቀቴን እና ልምዴን የበለጠ ማስፋት እንዳለብኝ አውቄ ነበር፡፡  በየ3 ወሩ የህክምና ቃላቶች እውቀቴን የሚያዳብር ኮርስ እወስዳለሁ ይሄም ከታካሚዎችና ከዶክተሮች ጋር በደንብ ለመረዳዳት ይረዳኛል፡፡  ታካሚዎችን እና እየተጋፈጡት ያለውን በሽታ በደንብ ለመረዳት በተደጋጋሚ በተለያዩ የካንሰር አይነቶች ጉዳይ የሚደረጉ የትምህርት መድረኮችን ላይ እሳተፋለሁ፡፡
 
<<ጥሩ አድማጭ መሆን መቻል ታካሚዎችን ለመረዳት በጣም ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ በዚህም ለነሱ በድንብ እርዳታ እንድሰጥ ያስችለኛል፡፡ ምንም እንኳን ከስራ ሰአቴ በተጨማሪ ብሰራም ወይም በጣም ከመሸ በኋዋላ ከአንዳንድ ታካምዎች ሲደወልልኝ ብመልስላቸውም ከዚህ በላይ ለማድረግ እና የእነሱን ምቾት ለመጠበቅ ፈቃደኛ ነኝ፡፡  በቻልኩት የራሴ ትንሽ መንገድ የተሻለ ስሜት እንዲሰማቸው ማድረጌ በራሴ እንድኮራ ያደርገኛል፡፡>> በማለት ፓኒታ አብራርታለች፡፡
 
For more information please contact:

Related Packages

Related Health Blogs