bih.button.backtotop.text

በሆራይዘን የህክምና ማዕከላችን በእራስዎ የበሽታ መከላከያ ስርዓት የሳንባ ካንሰርን ለመፈወስ ብሩህ ተስፋ አለ፡፡

ሴፕቴምበር 10, 2019

“የቅርብ ጊዜ ምርምር እንዳሳየው የimmunotherapy ህክምና በመሰራጨት ላይ ያለ የሳንባ ካንሰር ያለባቸውን በሽተኞች በሕይወት የመኖርን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር ያሳያል ፣ይሄም ለታካሚዎችና ለህክምና ባለሙያዎች ትልቅ እምርታ ነው።“

ይህንን እያነበቡ ከሆኑ ስለ የimmunotherapy  ሰምተው ያውቁ ይሆናል ፡፡ ግን immunotherapy ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉ?

በአጭሩ ፣የimmunotherapy የሰውነትዎን በሽታ የመከላከል ስርዓት ካንሰርን እንዲዋጋ የሚረዳ ነው ፡፡ የimmunotherapy ህክምና ለብዙ በሽታዎች ቀድሞውኑ የነበረ ቢሆንም ፣ በmetastasis ደረጃ  ማለትም የካንሰር ሕዋሳት ከጀመሩበት የሰውነት ክፍል ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል የመሰራጨት ደረጃ ላይ የደርሰባቸው የሳንባ ካንሰር ታካሚዎችን የመዳን እንደሚጨምር የቅርብ ጊዜ ምርመራ ያሳያል።  ይሄም የካንሰር በሽታን እየተዋጉ ላሉ ታካሚዎችና የህክምና ባለሙያዎች ትልቅ ጥቅም አለው።

የሳንባ ካንሰር በዓለም ዙሪያ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸውን በሽተኞች ያጠቃል፡፡ የሳምባ ካንሰር በሁለት ምድቦች የሚከፈል ሲሆን እነዚህም ፣  የአነስተኛ የሕዋስ ሳንባ ነቀርሳ (ኤስ.ሲ.ሲ) እና አነስተኛ ያልሆነ ህዋስ ሳንባ ነቀርሳ (ኤን.ኤስ.ሲ.ሲ.) በመባል ይታወቃሉ። ሁለተኛው አይነት ካንሰር ከሁሉም የሳንባ ካንሰር በሽተኞች እስከ 80% የሚደርስ ነው፡፡

ከዚህ በፊት የimmunotherapy ሕክምና የታካሚውን በሽታ የመከላከል ስርዓት በቀጥታ የካንሰር ሕዋሳት ላይ በቀጥታ እንዲያጠቃ ለማነቃቃት በሚረዳ መድኃኒት ላይ ብቻ የተወሰነ ነበር ፡፡ በቅርብ ጊዜ የተደረገ ምርምር የተወሰኑ የካንሰር ሕዋሳት ከህክምናው ጥቃት እንዲተርፉ በማድረግ የሳንባ ካንሰር በሽተኞች በሽታ የመከላከል ስርዓትን እንቅስቃሴ በመከላከል ወይም “በማቆም” ሚና የሚጫወተውን protien PD-1 የሚባለውን አግኝቷል ፡፡

ይህ ግኝት ለሳንባ ካንሰር ሕክምና አዳዲስ ዕድሎችን አስገኝቷል አሁን የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓት በካንሰር ሴሎች ላይ በቀጥታ እንዲያጠቃ ከማድረግ በላይ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓቱ የካንሰር ሕዋሳትን ሙሉ በሙሉ ከመግደል ወደኋላ እንዲል የሚያደርገውን ፕሮቲን ማጥፋት ተችሏል ፡፡ ይህም በሽታን የመከላከል ስርዓቱ የካንሰር ሕዋሳቱን ያለ ምንም ችግር የሚያጠፋበትን መንገድ ይፈጥራል።

ከዚህ አዲስ የሕክምና ዘዴ በስተጀርባ ያለው ሳይንስ - Immune Checkpoint Therapy  ተብሎ የሚጠራ ሲሆን – 2018 በበርኬሌይ ለካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ጄምስ አሊሰን እና ለኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ታኩኩ ሁንጆ በፊዚዮሎጂ ወይም በሕክምና መስክ በጋራ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

FDA አነስተኛ ያልሆነ ህዋስ ሳንባ ካንሰርን ጨምሮ የተለያዩ የካንሰር ዓይነቶችን ለመቋቋም በ ‹Immune Checkpoint Therapy› ውስጥ ያሉ የተለያዩ በርካታ ፀረ PD-1 እና የ ፀረ PD-L1 መድኃኒቶች እንዲጠቀሙ ፈቅዷል፡፡ አማራጮች pembrolizumab ፣ nivolumab ፣ atezolizumab ወይም durvalumabን ያካትታሉ።

የአሜሪካ ካንሰር ማህበር የእነዚህ መድኃኒቶች መተዋወቅ ለሳንባ ካንሰርን ህክምና አብዮታዊ የሆነ ነገር መሆኑን አስታውቋል ፡፡ ቀደም ሲል metastatic የሳምባ ነቀርሳ ካላቸው ታማሚዎች ውስጥ 5 ፐርሰንት የሚሆኑት ብቻ ከምርመራ በኋላ ለአምስት ዓመት ከበሽታው ነፃ ሆነው ይቆዩ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን በImmune Checkpoint Therapy pembrolizumab መዳኒትን በመጠቀም 5 ፐርሰንት ብቻ የነበረውን የታካሚዎች የመዳን ደረጃ እስከ 15-20 በመቶ እንዲያድግ ሆኗል፡፡ ከኬሞቴራፒ ወይም ከሌሎች የሕክምና ዓይነቶች ጋር ሲዋሃድ immunotherapy ለታካሚዎች የመኖር እድልን ይጨምራል ፡፡

Immunotherapy አነስተኛ ላልሆነ ህዋስ ሳንባ ካንሰር ዋና የህክምና አማራጭ ሆኗል። Immune Checkpoint Therapy መምጣት ለታካሚዎች የህይወት ጥራት እና ምቾት አዲስ እድልን ይፈጥራል፣ እናም ለተሟላ ማገገሚያ ታላቅ ተስፋን ይሰጣል ፡፡
For more information please contact:

Related Packages

Related Health Blogs