bih.button.backtotop.text

ስለ ካንሰር የአእምሮ አስተሳሰብ: አዎንታዊ አስተሳሰብ ነፃ ሊያደርግዎት ይችላል፡፡

‹‹አዎንታዊ አስተሳሰብ መከተል ከባድ የኑሮ ጫና የሚያስተካክል፣ ሁልግዜም ጤናማ አኗኗር መኖር እንደሚቻል የታመነ በመሆኑ በካንሰር በሽታ ቢጠቁ እንኳ ከዚህ አስቀያሚ በሽታ አንድ ቀን መዳን እንደምቻል እና በአግባቡ ከበሽታው ተፈውሰው መደበኛ ጤናማ ህይወት መምራት እንደሚችል እንድናምን ወይም እምነት እንዲኖረን ይረዳናል፡፡›› ይህ በአንዳንድ ወቅት በማይናመር የዩኒቨርስቲ መምህርት የነበረች እና የጡት ካንሰር ተጠቂ የነበረች ቲን ማይ ልዊን ስለካንሰር እንዴት ስታስብ እንደነበረች ከሰጠችው ማብራሪያ ተቀንጭቦ የተወሰደ ሲሆን ከዚያም ያጋጠማትን የጡት ካንሰር ታክማ መዳን እንደምትችል በሙሉ ልቧ በመተማመን ለህክምናው ወደ ሆራይዘን ክልላዊ የካንሰር ህክምና አገልግሎት ለመሄድ መርጣለች፡፡  ቲን ማይ ልዊን በያንጎን ዩኒቨርስቲ እ.አ.አ እስከ 2008 ድረስ የኮምፒውት ጥናት ፕሮፌሰር ወይም መምህርት በመሆን አገልግላለች፡፡ በዚህው ጊዜ ነበር በሰውነት ውስጥ እንግዳ ስሜት የተፈጠረባት፡፡ በወቅቱም በጡት በኩል ተራ እንግዳ ስሜት እንደተሰማት በመቁጥር የባህላዊ ህክምና አገልግሎት መከታተል ጀምራለች፡፡ በመጀመሪያ ጊዜ ሕክምናውን እንደ ጀመረችም ሕክማነው ውጤታማ መስሏት የነበረ ሲሆን በወቅቱ የተሸለ መስሏት የነበረው የበሽታው እድገት ስለጠፋ ቢሆንም ግን፣ ለዓመት ያህል እንደገና ተመልሰው አገረሸባት፡፡ በመጨረሻም አንዲት የቀዶ ሕክምና ጓደኛዋ ሙሉ የጤና ምርመራ እንድታደርግ በሞከረችው መሰረት ተመርምራ የጡት ካንሰር እንደያዛት ከምርመራ ውጤቱ ለማወቅ ችላለች፡፡ 
 
 
የጤና ምርመራ በማድረግ በምርመራው ውጤት መሰረት የጡት ካንሰር እንደያዛት ማረጋገጧም ከባድ ድንጋጤ ሊያስከትልባት እንደሚችል ማንም በቀላሉ መገመት የሚችል ሲሆን፣ ሁኔታውም ከዩኒቨርስቲው የነበራትን ይዞታ እንድትለቅ የሚያስገድዳት መሆኑ በቀላሉ መገመት የሚቻል ጉዳይ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ግን ሙሉ በሙሉ በራሷ እምነት እንደቀላል ነገር በመውሰድ ሙሉ በሙሉ እንዳላመማት በቀላሉ ራሷን ማሳመን መርጣለች፡፡ ‹‹በእርግጥ በጉዳዩ እና በምርመራ ውጤቱ አንዳች መጥፎ ነገር እንዳጋጠመኝ አውቄአለሁ፡፡ ሆኖም ግን የጠየና ምርመራ አድርጌ የጡት ካንሰር እንዳለብን ካወቅሁ በኋላ ስለጉዳዩ ምንም እልተሰማኝም ነበር፡፡ ነገር ግን በፍፁም እንግዳ ስሜቱ ሙሉ በሙሉ ተገርሜለሁ፡፡ በማለት በጫወታችን ወቅት ስለነበራት አዎንታዊ አስተሳሰዋን አብራርታልናለች፡፡ ‹‹ በፍፁም እያመመኝ እንዳልሆነ ሁሉ ማሰቡን ማቆም አልቻልኩም ስለክስተቱ እንግዳነት ተገዥ ዌም ምርኮኛ መሆኔንም የበለጠ ማሰብ ጀመርኩኝ፡፡ በእርግጥ አሞኛል፣ የካንሰር በሽታ ይዞናል ብዬ ራሴን በፍፁም አላጨናነኩም ነበር፡፡›› በማለት አብራርታለች፡፡ 
 

እውነተኛ ህይወት ያጎናፅፈኛል

 
‹‹ጓደኛዬ ወደ ታይላንድ ሄጄ የህክምና አገልግሎት ማግኘት እንዳለብን ስትነግረን ወዲውኑ የተሸለ ስሜት አደረብኝ፡፡ በእርግጥ ስለ ቡምሩንግራድ ሆስፒታል የሕክምና ዝና ሰምቼ ስለነበር ስለጉዳዩ ብዙም መጨነቅ አላስፈለገኝም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተሸለ ስሜት እና በራስ መተማመን ስለታላንድ ሕክምና ጉዳይ የተደሰትኩት ለግብይት ወደባንኮክ ለመሄድ ተዘጋጅቼ ስለነበር እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ከተማውን በጣም እወደዋሉ፤ ወደዚህ መምታትም ከሚገባው በላይ ያስደስተናል፡፡›› በማለት ገልፃለች፡፡ 
 
ምንም እንኳ አእምሮዋን በቀላሉ ማሳመን የቻለች ቢሆንም ግን ህክምናው ለከባድ ፈተናዎች አልተከናወነም፡፡ ከሕክምናው ፈተናዎች ውስጥ አንዱ የካንሰሩ በሽታ በፍጥነት በአጥንቶች ውስጥ መሰራጨት ነበር፡፡ በወቅቱ ስለሕክምናው ሂደት በበላይነት ሲመራ የነበረው የኦንኮሎጂስት ሕክምና ባለሙያ የሆኑ ዶክተር ቪናኦ አይራፕራካይ በአንድ ወቅት እሷ በጭራሽ ያልጠበቀችውን ነገሯት፡፡
 
‹‹ዶክተር ቪናይ አይራፕራካይ በሽታው በነርቮች እና በአትንቶች መሰራጨ,ቱን ከገለፁላት በኋላ ለመኖር ያለን እድል ስድስት ወራት ብቻ እንደሆነ ነገሩኝ፡፡ ምንም እንኳ ዶክተሩ በነገሩኝ ነገር በተወሰነ መልኩ ድንጋጠተ የተሰመኝ ቢሆንም፣ የመጣውን ሁሉ በጸጋ ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭ ስላማይኖረኝ ራሴን አረጋግቼ ተቀበልኩት፡፡›› በማለት አብራርታለች፡፡ 
 

በከፊል ማሸነፍ፣ በከፊል ውድቀት 

 
‹‹የተደረገልኝ እንክብካቤ መገመት ከማይቻለው በላይ የነበረ ሲሆን ሙሉ በሙሉም ሙያዊ እንክብካቤ ነበር፡፡ በሕክምናው ወቅት የተወመደቡልኝ ነርሶች ያደረጉልኝ እንክብካቤ እና የአስተርጓሚው ከፍተኛ ብቃት በአስተማማኝ እጆች ላይ እንደሆንኩኝ ተሰምቶኝ እንደጤነኛ ጊዜ በቃላት መናገር ከምችለው በላይ ደስ ብሎኝ ነበር፡፡›› በማለት ቲን ማይ ልዊን አስታውሳናለች፡፡ የህክምናው ሂደት በሶስት ዙር የኮምቴራፒ ወይም የኬሚካል ሕክምና መስጠት የተጀመረ ሲሆን፣ በዚህ የሕክምና ሂደትም የካንሰር ሀኪም ወይም አንስሎጂስቱ ለቀዶ ጥገና ሕክምና አስፈላጊውን ሁሉ ለማመቻቸት እና ዝግጁ ለማድረግ እንዲቻል በየጊዜው ሶስት ጊዜ ኬምቴራፒ ወይም የኬሚካል ሕክምና ወኪሎችን መቀየር አስፈላጊ ነበር፡፡ ‹‹በወቅቱም ራሴን ለሕክምናው በቁርጠኝነት ሰጥቼ ስለሕክምናው በሐኪሞች ሙሉ እምነቴን ጣልኩባቸው፡፡ ሐኪሞቹም በዚህው መሰረት በተሳካ መልኩ የካንሰሩን ግንድ ያስወገዱ ሲሆን፣ እና የጨረር ህክምናው እንደተጠበቀው የተከናወነ ሲሆን የቆዳ ንቅለ ተከላው አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ይህን ተከትሎም ከሆዴ ላይ ቆዳ ለመውሰድ በቅተዋል፡፡ እንደ መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ የቆዳ ንቅለ ተከላው ሂደት በሚከናወንበት ወቅት ሌላኛው ጡቴ እንዲወገድ ተደርጓል፡፡
 
አቅልሎ ማሰብ ከበሽታው መዳን እንዲቻል ይረዳል ለህክምናው ከፍተኛ የመንፈስ ጥንካሬ እና ቁርጠኝነት ያመነችበት በመሆኑ ምንም አይነት በህክምናው ምክንያት ስጋት ሳይገባት እና አላስፈላጊ የአስተሳሰብ ጫና በማስወገድ ስለተቀበለች ቲን ሜን ሉዊን ስለ የጡት ካንሰር ህክምናዋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡ አስተሳሰባችን በተለይ በህክምና ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ በማንኛውም ህክምና እናድናለን ብለን እራሳችንን ካሳመንን በቀላሉ መዳን እንችላለን፡፡ በእውነቱ ከሆነ ማድረግ የማትፈልግ ከሆነ ላታደርግ እንደምትችል እመነኝበማለት በሳቅ ጭምር አብራርታለች፡፡ 
 
እኔ ደስተኛ ህይወት ለመኖር እመርጣለሁ፡፡ በወቅቱ በልብ ህመም በሽታ እና ለደም ግፊት ስሰቃይ በነበርኩበት ጊዜም ራሴን አረጋግቼ ደስተኛ ህይወትን ለመኖር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ምንም አይነት ከበሽታው ጋር ተያይዞ ህይወቴ ላይ ጫና እንዳይፈጠር ለማድረግ ችያለሁ፡፡ በሆስፒታል ባድረግኩት ህክምና ከበሽታዬ ለመፈወስ የቻልኩ ሲሆን በወቅቱ በአካባቢው ወይም በሆስፒታሉ አቅራቢያ ወደሚገኙ ሱቆች በመሄድ አንዳንድ ሸመታዎችን ለማድረግ እንድችል ነርሶችን እለምናቸው ነበር” በማለት አብራርታለች፡፡ በዚህ መሰረት ቲን ሜን ሉዊን ለሌሎች ታካሚዎች የምታብራራው ሀሳብ፡- ለካንሰር በሽታ ቦታ አትስጡ እንዲያሸንፋችሁ አትፍቀዱ፡፡ ሙሉ በሙሉ ከውስጣችሁ ሊጠፋ እንደሚችል እመኑኝ፡፡ ከዚያ በኋላም በህክምናው ሂደት ወቅቱ ሀኪሞች የሚነግሯችሁን ሁሉ ከማድረግ ውጪ ሌላ ምንም አይነት አያይዛችሁ አታስቡ፡፡ ቲን ሜይ ሉዊን በወቅቱ ቃለ መጠይቅ ያደረገችልኝ በፍፁም ፈገግታ ነበር፡፡ እና ቃለ መጠይቁን ያደረገችልኝ ከአውሮፓ ከገበያ ስትመለስ ነበር፡፡ 
For more information please contact:

Related Packages

Related Health Blogs